top of page

General Information - Amharic

Holding Hands

ስለ ኤች. አይ. ቪ. እና ኤድስ በግልጽ እንወያይ

ኤች ኣይ ቪ ኤድስ፡ማለት ሕዩማን ኢሙኖ ዴፊሸንሲ ሲንድሮም የሚባል የቫይረስ ስም ሲሆን፣ ኤድስ ኤች.እይ.ቪ. የሚያደርሰው  የመጨረሻ ደረጃ ወይም የበሽታው ስም ነው። ኤች አይ ቪ በደሙ ውስጥ ያለበት ሰው ኤድስ በሽታ ደረጃ ላይ ለመድረስ ብዙ አመታት ሊወስድበት  ይችላል። ይኸውም መዳኒቱንም ሳይጀምር የኤች.አይ፣ቪ፣ ቫይረስ በደሙ እያለ ለብዙ አመት ሊቆይ ይችላል። አንድ ሰው የኤድስ በሽታ ደረጃ ላይ ደረሰ ማለት የኤች.አይ.ቪ .ቫይርስ የአካላችንን የተፈጥሮ የበሽታ መከላከያ ሃይል ተቁዋማትን ደምስሶ፣  ሰውነታችን ከማንኛውም በሽታ የመቋቋም ሃይሉን በማዳከም፣ ለተለያዩ ኢንፈክሽኖች ይጋለጣል ማለት ነው። አንድ ሰው አንድ ወይም ሁለት ኢንፌክሽኖች ሲኖሩበት እና በጣም ዝቅ ያለ የቲ-ሴል ቁጥር(የአካላችን የተፈጥሮ የበሽታ መከላከያ) ሲኖረው ያሰው በኤድስ  በሽታ ደረጃ ደረሰ ሊያስብለው ይችላል።

ኤችአይቪ (በእንግሊዘኛ ቋንቋ: Human Immunodeficiency Virus (HIV) ህዩማን ኢምዩኖደፊሸንሲ ቫይረስ) በመባል የሚታውቅ ቫይረስ ነው። ኤችአይቪ ቫይረስ የሰውነትን የበሽታ መከላከያ ኋይል፣ በተለይ ነጭ የደም ሴሎችን (ህዋሳትን) በማጥቃት በቀላሉ ሰውነት ለበሽታ እንዲጋለጥ የሚያደርግ አደገኛ  ቫይረስ ነው። ኤች.አይ.ቪ. ያለባቸው ሰዎች የበሽታው ምልክት ሳይታይባቸው ለብዙ አመታት መኖር እንደሚችሉ ከዚህ በላይ ተገልጿል።  ቫይረሱ በሰውነት  ውስጥ እስከ አስር ዓመትና ከዚያም በላይ  በመቆየት፣ ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳይታይበት በመኖር፣  እና  ይህንም         ባለማውቅ  በዚህ ሁኔታ ቫይረሱ በደሙ ያለበት  ሰው ቫይረሱን ወደሌላ ሰው ሊያስተላለፍ የሚችልበት እድል ሰፊ ነው።

በኤች አይ ቪ ሊያዝ (ሊጠቃ)  የሚችለው ማን ነው ?

ኤችአይቪ (በእንግሊዘኛ ቋንቋ: Human Immunodeficiency Virus (HIV) ህዩማን ኢምዩኖደፊሸንሲ ቫይረስ) በመባል የሚታውቅ ቫይረስ ነው። ኤችአይቪ ቫይረስ የሰውነትን የበሽታ መከላከያ ኋይል፣ በተለይ ነጭ የደም ሴሎችን (ህዋሳትን) በማጥቃት በቀላሉ ሰውነት ለበሽታ እንዲጋለጥ የሚያደርግ አደገኛ  ቫይረስ ነው። ኤች.አይ.ቪ. ያለባቸው ሰዎች የበሽታው ምልክት ሳይታይባቸው ለብዙ አመታት መኖር እንደሚችሉ ከዚህ በላይ ተገልጿል።  ቫይረሱ በሰውነት  ውስጥ እስከ አስር ዓመትና ከዚያም በላይ  በመቆየት፣ ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳይታይበት በመኖር፣  እና  ይህንም         ባለማውቅ  በዚህ ሁኔታ ቫይረሱ በደሙ ያለበት  ሰው ቫይረሱን ወደሌላ ሰው ሊያስተላለፍ የሚችልበት እድል ሰፊ ነው።  

በኤች አይ ቪ ሊያዝ (ሊጠቃ)  የሚችለው ማን ነው ?

መልሱ ጥንቃቄ የጎደለው ማንኛውም ሰው ነው !

ኤድስ ማንንም ከማን ሳይለይ ጥንቃቄ የጎደለውን ሁሉ ሊጎዳ ይችላል ፦ ማለትም  ሴቶችን ፤-ወንዶችን ፡ግብረ ስዶማውያንን (ሆሞዎችን)፤ወጣቶችን ፣ አዋቂዎችን፣የሚወለዱ ጨቅላ ሕጻናትንም በአንድነት ሊያጠቃ ይችላል ፤

ማንኛውም ጥንቃቄ የጎደለው፣ኮንዶም አልባ የግብረ ሥጋ ግኑኝነት የሚፈፅም ሁሉ በቀላሉ በኤች .አይ .ቪ ቫይረስ ሊጠቃ ይችላል።

በኤች. አይ. ቪ. ቫይረስ እንዴት ልንያዝ እንችላለን ?

በኤች .አይ .ቪ. ቫይረስ  የመያዝ አደጋ የሚደርሰው፣ በቫይረሱ በደሙ ያለበት ሰው የዘር  ፈሳሽ ወደ  ብልቶች  ሲገባና፣ ወይም በቀጥታ በልዩ  ልዩ ሁኔታዎች ደም ከደም ለመቀላቀል ሲችል ነው።

የኤች.አይ..ቪ መተላለፊያ መንገዶች፦

ኤች.አይ.ቪ. ከማንም ሰው ጋር በምናደርጋቸው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች  ማለትም ለምሳሌ፣ እንደ እጅ መጨባበጥ፣ መተቃቅፍ፣ እና መሳሳም ሊያስተላልፉ እንደማይችሉና፣ በተጨማሪም ኤች አይቪ በመጸዳጃ ቤት መቀመጫ፣ በበር መክፈቻ፣ በመጠጫ ብርጭቆ ፣ በምግብ ወይም በማንኛውም አይነት ተመሳሳይ  ነገሮች አይተላለፍም በኣጠቃላይ በማህበራዊ ኑሮ ሊተላለፍ ኣይችልም። እንደ ቢንቢ  ትንኝ ንክሻ በመሳሰሉት  ምክንያትም ሊይዝ አይችልም። ቫይረሱ ከሰዉ ወደ ሰዉ እንጂ፡ ከሰዉ ወደ እንስሳ ወይ ከእንስሳ ወደ ሰዉ ሊተላለፍ ኣይችልም።

የሚተላለፈው በ3 ዋና ዋና መንገዶች ነው።

1.በወሲብ አማካኝነት ማለትም ያለ ኮንዶም በሚፈፀም ልቅ የሆነ የወሲብ(ግብረስጋ) ግንኙነት።

2.በደም አማካኝነት- ለምሳሌ በስሪንጋ( መርፌ)

3. ከእናት ወደ ፅንስ ይህ ደግሞ ፦ 1. በእርግዝና ወራት

3. በወሊድ (በሚወለድበት ) ጊዜ

4. በጡት አማኻኝነት ማለትም እናቱ ጡትዋን እምታጠባው ከሆነ ሊተላለፍ ይችላል።

ውስጣዊ ስስ ብልቶች ምን ምን ናቸው?

አይን፤ ፊት፤ እና አፍንጫ ፤ ወዋጫ ጎሮሮ ፤ የሴት ብልት ፤ የወንድ ብልት ፤ ፊንጢጣ ወይም የዓይነ- ምድር መውጫ  ናቸው ።

ከሴት ብልት የሚመነጭ ፈሳሽ ምንድ ነው?

የሴት ብልት (ቫጀና) ፦ ከሴት ብልት ውስጥ ተፈጥሯዊ  የሆኑ ብዙ ፈሳሾች ይመነጫሉ፡ የፈሳሹ አይነት ነጫጭ ወይም ጥርት ያለ ሲሆን ተግባሩም የሴቷን ብልት ከተለያዩ ብክለቶች የሚከላከል ነው።

የፈሳሹ ዓይነት ከሴት፣  ሴት እና  ከእድሜ ልዩነት የተነሳ  ሊለያይ ይችላል።

ግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚፈጠርበት ወቅት የፈሳሹ መጠን ይጨምራል ፣ይህም የሴቷን ብልት በማለሰለስ የወንዱ ብልት ወደ ሴቷ ብልት የሚገባበትን ሂደት ቀላል  እና  ምቹ  ያደርገዋል ማለት ነው።

 

በወር አበባ ወቅት የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለምን የበለጠ አደገኛ ሆነ?

የ ኤች አይ ቪ ቫይረስ በሴቷ ብልት ውስጥ ባሉት ፈሳሾች እና በደሟ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ስለሚገኝ በሽታውን የማስተላለፍ ዕድሉ ዕጅግ በጣም የላቀና አደገኛ  ነው።

በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ኮንዶም ማጥለቅ ያስፈልጋል!!!  በአጭሩ ከውጭ መጨረስ ብሎ ነገር አይሰራም!!!

ኤች. አይ .ቪ. ቫይረስ በግብረ ሥጋ ግኑኝነት ወቅት አዎ ይተላለፋል፣  ማለትም ወንዱ ወይም ሴቷ የዚህ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ያለ  ከሆኑ ።

ኤች አይ ቪ ሊተላለፍባቸው የማይችሉ መንገዶች ፦

•       የኤች አይቪ ቫይረስ ከሰውነት ከወጣ በኋላ በጣም ደካማ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ አይቆይም ወድያውኑ ይሞታል። በዚህ  የተነሳ ነው ኤችአይቪ ከማንም ሰው ጋር በምናደርጋቸው የዕለት ተዕለት ንክኪዎች  ለምሳሌ፣ እንደ እጅ መጨባበጥ፣ መተቃቅፍ፣ እና ጉንጭና ግንባርን መሳሳም አይስተላልፍም ። በተጨማሪም ኤች .አይ.ቪ. በመጸዳጃ ቤት መቀመጫ፣ በበር መኽፈቻ፣ በመጠጫ ብርጭቆ ፣ በምግብ ወይም በማንኛውም አይነት እንስሳ እንደ ቢንቢ ንክሻ በመሳሰሉት ሊተላልፍ  አይችልም።

የኤችአይቪ መተላለፊያ  ሁኔታዎች እንደሚከተለው ነው፦

•       ቫይረሱ ያለበት ሰው የተጠቀመበትን የሀሽሽ (ሳሚም) መርፌ ሌላ ሰው ደግሞ  ቢጠቀምበት (Intravenous) ቫይረሱ በቀጥታ ከደም ወደ ደም ሊተላለፍ ይችል።

•       ቫይረሱ ካለበት ማንኛውም ሰው (ወንድ ወይም ሴት) ጋር ያለኮንዶም የግብረ ሰዶም ግንኙነት (Homosexual, bisexual intercourse) በማድረግ በሽታው ሊይዝ /ሊተላለፍ ይችላል።

•       ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር በሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት (Heterosexual intercourse)

•       ኤች አይ ቪ ያለባት እናት ቫይረሱን (በእርግዝና ወራትና በወሊድ ጊዜ) ለሕፃንዋ ማስተላለፍ (Intrauterine, perinatal) ትችላለች።

•       ቫይረሱ ያለባት እመጫት ጡት ወተት ካጠባች ቫይረሱ ሊተላለፍ ይችላል።

ለኤድስ በሽታ መድኃኒት አለውን ?

በአሁኑ ጊዘ በኤችአይቪ ዙሪያ ላይ ብዙ መረጃዎችና እንክብካቤ  የሚገኝበት ጊዜ ስለሆነ የኤች.·አይ.·ቪ ቫይረስን አዳክሞና ተቆጣጥሮ አብሮ   ለመኖር ይቻላል። በአሁን ሰዓት ኤች.አይ.ቪን እንደማንኛውም አይንት ቫይረስ ቆጥሮ ሕክምናን በመከታተል ጤናን እየጠበቁና መንፈስን ሳያስጨንቁ ፣ተረጋግቶ መኖር ይቻላሉ።

ኤችአይቪ እንዳይዘን የምንከላከልበት ክትባት በአሁኑ ሰዓት የለም። ኤችአይቪ ከያዘም በኋላ የሚፈውስ መድኃኒት የለም። ነገር ግን ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖር ይቻላለ። በአሁኑ ጊዜ ፀረ-ኤችአይቪ መዳኒቶች ከፈተኛውን አስታውጾ በማድረግ ላይ የገኛሉ። ኤችአይቪ ያለበት ሰው በትክክል የፀረ-የኤችአይቪ መዳኒቶቹን በመውሰድ እንደማንኛውም ሰው ሥራን አየሠራ ኒሮውን መምራት ይችላል። ቫይርሱ ያለባቸው ሰዎች መውለድ ሲፈልጉ  ከጤና ባለሙያቸው ጋር በመነጋገር ተገቢውን የህክምና አገልግሎት  በመቀበል ጤነኛ ልጀ መውለድ ይችላሉ። ኤች.አይ.ቪ. ያለባት እናት ከማርገዝዋ በፊት ማወቅ የሚገባትን ቅድመ ዝግጅቶች  ጠንቅቃ ማወቅና መፈጸም  ይኖርባታል።

የኤች.አይ.ቪን መስፋፋት/መሰራጨት በጽኑ ስለመከታተል፦ መከላከል

•       መታቀብ (ከማንኛውም አይነት የግብረ ሥጋ ግንኙነት መቆጠብ) አንድ -ለአንድ የሆነ ተማማኝ የትዳር  ጛደኛ እስከሚያገኙ ድረስ በጥብቅ መጠንቀቅ ፣ "ያለኮንዶም፣ ዕምነት የለም "።

•       ሁለት ኤች.አይ.ቪ. እንዳለባቸው ያወቁ ባለትዳሮች፣ ወይም አበረው ያሉ ጉዋድኞች፣ በግብረ-ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ኮንዶም መጠቀም አለባቸው ፡፤ ምክንያቱም ከተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች ለመከላከል እና በተለያዩ የኤች.አይ.ቪ .ንዑስ ዝርያዎች ደግሞ ላለመጋለጥ እንዲረዳ ነው።

•       ከሁለት አንዳቸው ብቻ ከሆኑ ኤችአይቪ ያለበት ሁልጊዜ ኮንዶም መጠቀም እና ቅባት (Lubricant) ያለው ኮንዶም መጠቀም ግዴታ አለበት።

•       ከአንድ ሰው በላይ ጋር የግብረ-ሥጋ ግንኙንት የሚፈጸሙ ከነበሩ ወይም ከሆኑ፣ የኤች..አይ.ቪ .ምርመራ ያድርጉ!

•       ወንድ ከሆኑ እና ከወንድ ጋር የግብረ- ሰዶም ግንኙነት ፈፅመው ከሆነ ቢያንስ ቢያንስ በአመት አንዴ ይመርመሩ !

•       ሴት ከሆኑ እና ለማርገዝ እቅድ ካሎዎት ወይም ካረገዙ በአስቸኳይ ይመርምሩ (ጤነኛ ልጅ መውለድ ያስችልዎታል)

•       የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ከመፈጸሞ በፊት ስለ ኤችአይቪ እና ሰለ ተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች ከወንድ/ከሴት ጛድኛ ጋር በግልጽ መወያየት ልምድ ማረግ አለብን

•       በደንብ ተጠናኑ፣ ተወያዩ፣ ስለ ሁለታችሁም ስለ አለፈው ወሲባዊ ሕይወት ታሪካችሁ ተነጋገሩ፣ወይም በአደንዛዥ ዕጽ  ትጠቀሙ ከነበረ ፣ ስለ መጠጥ፣ ጫት ወዘተ  ተወያዩ፣

•       ከዚህ በፊት የኤች.አይ.ቪ. ምርመራ አድርገው እንደሚያቁና እንደማያቁ መጠያየቅ !

•       ምንም እንኳን የኤች.አይ.ቪ. እያዛለሁ ብለው ምንም ጥርጣሬ ባይኖሮትም፣ ሁልጊዜ  ለጠቅላላ ምርመራ በሚሄዱበት ወቅት  የኤች.አይ.ቪ. ምርመራ ቢያረጉ በጣም ጠቃሚ ነው !

•       በአንድ ወቅት ምርመራ ከአኤች አይ ቪ ነፃ መሆን ማለት፣ሁልጊዜም ነፃ አያደርግምና፣ ከተላያዩ ሰዎች ጋር የግረ-ሥጋ ግንኙነት ከዘወተሩ በየወቅቱ ይመርመሩ !

 

ስለኤች.አይ.ቪ. ምርመራ

እራስህን በርግጠኛ ለማወቅ፣  መልሱ የሚገኘው የኤች.አይ.ቪ .ምርመራን  በማድረግ ብቻ ነው። ስለዚህ እራስዎን የሚጠራጠሩ ከሆነ ይመርመሩ። 

 ተመርምረው ውጤትው ከቫይረሱ ነፃ ስለ መሆንዎ ቢነገሮትም፣አንዳንዴ" አጠራጣሪ   ውጤት" የሚባል ሁኔታ  (ዊንዶ ፔሬድ የሚባል)  ስላለ፣ ከ 2-3 ወር በኋላ እርግጠኛ ለመሆን ደግመው መመርመር ይገባል። ይህን እስኪያደርጉ ግን አሁንም ኮንዶም መጠቀሞን አይርሱ።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በሚከተለው ስ.ቁ እና አድራሻ ይጠይቁን

የእስራኤል ኤድስ መከላከያ ማህበራዊ አገልግሎት ድርጅት

ስለ ኤድስ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ካለዎት  ከታች በተጠቀሰው አድራሻ ጥያቄዎን በሙሉ ይላኩልን ወይንም በስ.ቁጥራችን ይደውሉ!

አድራሻችን፡ ርሆቭ ሃናፂቭ 18 ቴል-አቪቭ

ስ.ቁ 035613000 ቀጥታ መስመር 113  ፋክስ ቁ. 035611764

ኢሜል አድራሻ፦ lion@aidsisrael.org.il

ደብዳቤ ለመላክ ፓስታ ሳ.ቁ፣  57310 ቴል - አቪቭ 61572

የዐርዳታ መስመር በ ስ.ቁ  035613300( ከእሁድ - ማክሰኞ ከ20፡00-22፡00)

በእስራኤል የኤድስ መከላከያ ማህበራዊ አገልግሎት ድርጅት

በቴል-አቪቭ እና በብኤር ሸቫ ይገኛል ፣ለሁለቱም ከተሞች አድራሻዎችን

 

  ከዚህ በታች ይመልከቱ፦

ቴል-አቪቭ ፡ ርሆቭ ሃናፂቭ 18 ቴል-አቪቭ

ስ.ቁ 035613000 ቀጥታ መስመር 113

ከዕሁድ - ሐሙስ 17፡00-20፡00

 ማክሰኞና ኣርብ ከጠዋቱ 10፡00 -13፡00 ሊያገኙን ይችላሉ

ለስደተኞች በነጻ ነው

አርብ ፡ 10፡00-13፡00

ብኤር ሸቫ ፡ ርሆቭ ሚፃዳ 6\46 (መርካዝ ሀኔጌቭ)

ስ.ቁ ፡ 086486519 ቢደውሉ ሊያገኙን ይችላሉ

ሰኞ ፤ 18፡00- 20፡00

ሮብ ፡ 18፡00- 20፡00

ኢየሩሳሌም

ሮሆቭ ሃሶረግ 2  1ኛ ፎቅ

ዕሁድ 17፡00_ 20፡30

ሜይል hiv-clinic@joh.org.il

ስ/ቁ 0547132699

       058374428

“ተረም ክሊኒክ”

ኢንሹራንስ(ኩፓት ሆሊም) ለሌላቸዉ ስደተኞች ኣጠቃላይ ህክምና ይሰጣል

ሮሆቭ የርሚያሁ 80  ያሃቭ ህንጻ

ስ/ቁ 073225539

ሮብ 17፡00_20፡00

 *ኤች  ኣይ ቪ ለመመርመር ኣስቀድመዉ ደዉለዉ ቀጠሮ ይያዙ

 ኤድስን በጋራ እንከላከል!!

ከኤች .አይ .ቪ.. ነፃ የሆነ ትውልድን እንገንባ !

ከአሁኑ በእኛ ይብቃ፣ ለሌሎች አናሸጋግር ሰቆቃ !

እናንተ ሰቆቃውን እያወቃችሁ፣እንዴት ይህን ለሌላ አሻገራችሁ ?

በምድር ነውሩን ያወቀ፣ በሰማይም ፀደቀ !

ይሉኝታን ያወቀ፣ ለወገኑ ተጨነቀ !

bottom of page